top of page

ግማሽ ሙሉ ወይስ ግማሽ ጎዶሎ


ጫማዎችን በማምረትና በመሸጥ የተዋጣለት አንድ ኩባንያ ነበር::አንድ ቀን አመራሩ ገበያውን ወደ አፍሪቃ ለማስፋፋት ይወስንና የገበያ ጥናት እንዲያካሂድ አንድ ከፍተኛ የሽያጭ ሰራተኛውን ይልኩታል:: አፍሪቃ ሲደርስም አብዛኛው ህዝብ ያለጫማ እንደሚሄድ ማየት ቻለ:: ቀጥሎም "መጥፎ ዜና እዚህ ጫማ የሚያደርግ ሰው ፈጽሞ የለም!" ሲል ወደ ዋናው መስሪያቤት ፋክስ ላከ:: ሲመለስም አፍሪቃ ውስጥ ጫማ መሸጥ አዋጪ እንዳልሆነ በአካል ቀርቦ ሪፖርት አደረገ:: የፋብሪካው አመራር የሁለተኛ ሰው አስተያየት ማከሉ ጥሩ እንደሚሆን ስላመነበት ሌላ የሽያጭ ሰራተኛውን ይልካል:: አፍሪቃ ሲደርስም ባየው በጣም ስለተደነቀ ሁለተኛው ልኡክ የሚከተለውን መልእክት በአስቸኳይ ፋክስ አደረገ:-"በጎ ዜና እዚህ ጫማ የሚያደርግ ሰው ፈጽሞ የለም!" ቶሎ ተመለሰና ለስራ አመራሩ" የተከበራችሁ! ሆይ በጣም ሃብታም ልንሆን ነው እና እንኳን ደስ አላችሁ አፍሪቃ ውስጥ ትልቅ የጫማ ገብያ ነው ያለው:: ማድረግ የሚጠበቅብን ነገር ቢኖር ጫማ ስለማድረግ ጥቅምና አስፈላጊነት ህዝቡን ማስተማር ብቻ ነው::"

ህይወት እንዳየናት ናት:: ማንኛውንም ነገርና ሁኔታ አዎንታዊና አሉታዊ ገጽታዎች አሉት:: ኩባያውን "ግማሽ ሙሉ" ወይም "ግማሽ ጎዶሎ" ብሎ መግለጽ ይቻላል:: ምርጫው ያንተና ያንተ ብቻ ነው:: አንድ ማስታወስ ያለብህ ነገር ግን አለ: ምርጫህ ለስኬትህም ሆነ ለውድቀትህ ምክንያት እንደሚሆን::


16 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page