top of page

አንተው ራስህ ነህ


በአንድ ድርጅት ውስጥ አንድ ቀን እንዲህ ሆነ:: ከምሳ በኋላ ሰራተኞች ወደ ቢሮአቸው ሲመለሱ የሚከተለው ማሳሰብያ መግቢያ በር ላይ ተጽፎ አገኙ::

"እዚህ ድርጅት ወስጥ ስትሰሩ እድገታችሁን ሲያሰናክል የነበረው ሰው ትናትና ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል: ከዘጠኝ ሰአት ጀምሮ ወደ ድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመምጣት ሬሳውን መሰናበት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::"

መጀመርያ ላይ አንድ የስራ ባልደረባቸው በመሞቱ ሁሉም ሃዘን ተሰማቸው::ቆይቶ ግን ይህ ሰው ማን እንደሆነ ለማወቅ ሁሉም ጓጉ:: ሁሉም ሰው ግን በውስጡ "ማን ነው እድገቱን ሲያሰናክል የነበረው ሰው?" እያለ ያስብ ነበር::

ሰአቱ ደርሶ ሁሉም በየተራ እየመጡ በሬሳ ሳጥኑ ውስጥ ያለውን ሰው ማየት ጀመሩ:: ይሁን እንጂ ሁሉም ባዩት ነገር በመደናገጥ አፋቸውን ከፍተው በጸጥታ ተዋጡ::ልክ አንድ ሰው ውስጣዊ መንፈሳቸውን የነካ ይመስል በአድናቆት ተዋጡ::

የሬሳ ሳጥኑ ውስጥ አንድ መስታወት ነበረ::ወደ ውስጥ ያየ ሰው ሁሉ የራሱን ፊት መልሶ ያይ ነበር::ከራሱ ምስል በታችም የሚከተለው ጽሁፍ በግልጽ ይታይ ነበር::" በእድገትህ ላይ መሰናክል በማስቀመጥ ሊገታህ የሚችል አንድ ሰው ብቻ ነው እሱም አንተ ነህ::

አንተ ብቻ ነህ ህይወትህን ከስሩ መለወጥ የምትችለው::

አንተ ብቻ ነህ በደስታህ በስኬትህ በአስተሳሰብህና አመለካከትህ ላይ በጎ ተጽእኖ ማሳደር የምትችለው:: አንተ ብቻ ነህ ራስህን ማገዝ ከውድቀት ማንሳት የምትችለው::

አለቃህ ድርጅትህ ወላጆችህ አጋርህ ጓደኛህ ሊለወጥ ህይወትህ አይለወጥም:: ህይወትህ የምትለወጠው አንተ ስትለወጥ ብቻ ነው::ከነዛ ጎታችና አጋች እምነቶችህና አስተሳሰቦችህ ስትላቀቅና ለህይወትህ ኃላፊነት ያለብህ አንተና አንተ መሆንህን ስታውቅ ህይወትህ ለበጎ ትለወጣለች::

በዶ/ር ተስፋይ ሰለሞን::

33 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page