top of page

የሚሸጡ ቡችሎች




በአንድ ሱቅ በር ላይ "የሚሸጡ ቡችሎች እዚህ አሉ" የሚል ምልክት ተሰቅሏል:: እንዲህ አይነት ምልክቶች በተለይ ህጻናትን ለመሳብ አይነተኛ ዘዴዎች ናቸው::አንድ ትንሽ ልጅም ወደ ሱቁ መጥቶ" ቡችሎችን በስንት ነው የምትሸጡት? " ሲል ጠየቀ:: የሱቁ ባለቤትም " ከ30 እስከ 50 ብር" ሲል መለሰለት ልጁም ኪሱን በረበረና ያሉትን ዝርዝር ሳኒቲሞች አወጣ"ሁለት ብር ከ37 ሳንቲም አለኝ:: ቡችሎችን ማየት እችላለሁ?" አለ የሱቁ ባለቤትም ፈገግ አለና ሲያፏጭ አንዲት ውሻ አምስት የሚያምሩ ቡችሎች አስከትላ ብቅ አለች:: አንደኛው ቡችላ ከሁሉም ኋላ ቀርቶ ቀስ እያለ እየመጣ ነው:: ወዲያው ትንሹ ልጅ ቀስ እያለ እግሮቹን እየጎተተ የሚመጣውን ቡችላ አይኑን ሳበው:: "ያ መጨረሻ ያለው ምን ሆኖ ነው?" ሲል ጠየቀ:: የሱቁ ባለቤት ቡችላው የእንስሳት ሃኪም መርምሮት ሽንጡ አከባቢ መገጣጠሚያው የታመመ መሆኑን ነግሮኛል:: "ሁልጊዜም ሽባ ሆኖ መኖሩ ነው" አለው:: ትንሹ ልጅ ተደነቀ:: "መግዛት የምፈልገው እርሱን ነው::" አለ::  የሱቁ ባለቤትም "አይ አይሆንም ያንን ቡችላ መግዛት አያስፈልግህም የእውነት ከፈለከው እንዲሁ እሰጥሃለሁ::" አለው ትንሹ ልጅ ተቆጣ:: ቀጥታ የሱቁን ባለቤት አይኖች እየተመለከተ እንባ እየተናነቀው እንድትሰጠኝ አልፈልግም::ይህ ትንሽ ውሻ ልክ ሌሎቹ የሚያወጡትን ዋጋ ያህል የሚያወጣ ነው:: ሙሉ ዋጋውን እከፍልሃለሁ:: አሁን 2 ብር ከ37 ሳንቲም እስጥሃለሁ: ከዚያ ዋጋዮን ከፍዮ እስክጨርሽ በየወሩ 50 ሳንቲም እከፍልሃለሁ::" አለ የሱቁ ባለቤት ለምን አትሰማኝም አንተልጅ "ይህን ትንሽ ውሻ መግዛት ይቅርብህ እንደሌሎቹ ቡችሎች መሮጥ መዝለልና ከአንተጋር መጫወት አይችልም::" ይህንን ሲናገር ትንሹ ልጅ የለበሰውን ሱሪ አንደኛውን እግር ከፍ አድርጎ ክፉኛ የተጣመመና በትልቅ የብረት ማቀፍያ የተደገፈ ሽባ እግሩን አሳየው:: ከዚያ የሱቁን ባለቤት ቀና ብሎ ተመለከተና ቀስ ባለ ድምጽ " እኔም በደንብ መሮጥ አልችልም እና ትንሹ ቡችላም ህመሙን የሚረዳለት ሰው ያስፈልገዋል::" ሲል መለሰለት::

37 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page