top of page

የሰርከስ ሰልፉ


አንድ ጊዜ በአስራዎቹ እድሜ ክልል ሳልሁ እኔና አባቴ ወደ ሰርከስ ለመግባት ቲኬት ለመግዛት ወረፋ ይዘን ቆመን ነበር:: በመጨረሻ በትኬት ቆራጯ መካከል የቀረው አንድ ቤተሰብ ብቻ ነበር::

እነዚህ ቤተሰቦች በጣም አስገርመውኝ ነበር:: ስምንት ልጆች ናቸው:: ምናልባት ሁሉም ከ12 አመት በታች ሳይሆኑ አይቀሩም:: ብዙ ገንዘቦች የሌላቸው መሆናቸውን መናገር ይቻላል:: ልብሶቻቸው ውዶች አይደሉም::ግን ንፁህ ናቸው:: ሁሉም ሁለት ሁለት በመሆን እጅ ለእጅ ተያይዘው ከወላጆቻቸው ጋር ቆመዋል:: በጣም ስርዓት ያላቸው ልጆች ነበሩ::በዚያ ምሽት ሰለሚያይዮዋቸው ሰርከስ: ዝሆኖችና ሌሎች ድርጊቶች በመደነቅ እያወሩ ነው:: ከዚህ በፊት ሰርከስ አይተው እንደሚያዉቁ ያስታውቃል የልጅነት ህይወታቸው ማድመቅያ ነበር::

አባትና እናትየው ኮራ ብለው ቆመዋል:: እናትየው የባሏን እጅ ይዛ ቀና ብላ ስታየው "አንተ የእኔ ጀግና ነህ::" የምትለው ትመስል ነበር:: እሱም ፈገግ ብሎ በኩራት ሲመለከታት " ትክክል ነሽ::" ብሎ እየመለሰላት ይመስላል::

ቲኬት ቆራጯ አባትየውን ስንት ቲኬት እንደሚፈልግ ጠየቀችው ::ኮራ ብሎ " እባክሽ ለስምንት የልጆችና ሁለት የአዋቂ ቲኬቶች ስጪኝ::" አላት ቲኬት ቆራጯ ዋጋውን ነገረችው::

የሰውየው ሚስት እጁን ለቀቀችውና ጭንቅላቷን ወደ መሬት አቀረቀረች:: የሰውየው ከንፈር መንቀጥቀጥ ጀመረ:: ሰዉየው ወደ ትኬት ቆራጯ ዝቅ ብሎ " ስንት ነበር ያልሽው?" ሲል ጠየቃት::

ቲኬት ቆራጯ እንደገና ዋጋውን ነገረችው::

ሰውየው በቂ ገንዘብ አልነበረውም::

ይህ ሰው እንዴት ብሎ ዞሮ ለልጆቹ በቂ ገንዘብ ስለሌለው ሰርከሱ ሊያስገባቸው እንደማይችል ይንገራቸው?

ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሲመለከት አባቴ እጁን ኪሱ ውስጥ ከተተና የ20 ዶላች ኖት አውጥቶ መሬቱ ላይ ጣለው:: በዚያን ወቅት እኛም ሃብታም አልነበርንም : ከዚያ አባቴ ጎንበስ ብሎ ከመሬቱ ላይ ብሩን አነሳና የሰውየውን ትከሻ ነካ አደረገ:: ከዚያ "ጌታዮ ይቅርታ ይሄ ብር ከኪስህ ወድቆ ነው::" አለው::

ሰውየው ምን እንደተካሄደ ገብቶታል::እርዱኝ ብሎ አልነመነም: ነገር ግን በዚህ ተስፋ የሚያስቆርጥ : ልብ የሚሰብርና የሚያሳፍር ሁኔታ ውስጥ እርዳታውን አመስግኖ ተቀበለ:: የአባቴን አይኖች በቀስታ ተመለከተ: የአባቴን እጅ በሁለቱ እጆቹ ያዘ: 20 ዶላር የያዘበትን የአባቴን እጅ አጥብቆ እንደያዘ ከንፈሩ እየተንቀጠቀጠና እይኖቹ እምባ ተሞልተው" አመሰግናለሁ: አመሰግናለሁ ጌታዪ:: ይሄ ለእኔና ለቤተሰቤ በጣም ትልቅ ነገር ነው::" አለ

እኔና አባቴ ወደ ወኪናችን ተመልሰን ወደ ቤት ተጓዝን:: በዚያ ምሽት ወደ ሰርከስ አልሄድንም : ግን ሰርከስም ሳናይም አልሄድንም::

ዳን ክላርክ:: የዶሮ መረቅ ለነፍሴ


10 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page