top of page

ያረከውን ሰው እንዳይሰማው

አንድ ደግ ሰው በፈረስ ከሩቅ ሃገር ወደ መንደሩ ሲመለስ በጫካ ውስጥ አንድ ሌባ ሰው የታመመ በመምሰል ጌታው አትለፈኝ እባክህ ከባድ የሆነ ሆድ ቁርጠት ይዞኛል በምትወደው ከዚህ ጥለሀኝ ከሄድ እየመሸ ስለሆነ አውሬ ይበላኛል ብሎ ይማጸነዋል:: ደጉም ሰው ያዝንለትና አይዞክ ወንድሜ ብሎ ከፈረሱ ላይ ተሸክሞ ያወጣዋል የፈረሱንም ሉጋም ይዞ በእግሩ ፊት ፊት ይመራዋል ሌባውም ጌታው በግርህ ለራስክ ከመሄድ ይልቅ የፈረሱን ልጓም ይዘክ ስትመራኝ ጀንበር እያዘቀዘቀች ስለሆነ እንቅፋት ይመታካል:: ተሰናክለክም ብትወድቅ ጉዳት ይሆናልና እርካቡን አስቆንጥጠሀኝ ሉጋሙን አሲዘኝ ቀስ እያልኩ አዘግማለው ይለዋል:: የፈረሱም ባለቤት በየዋህነት ፈረሱን ለሌባው ይለቅለታል ይን ጊዜ ሌባው ፈረሱን ኮርኩሮ ሉጋሙን አላልቶ ሽምጥ ጋለበ: በስላቅም እንግዲህ ደህና አምሽ ጌታው ብሎ ተፈተለከ ሲጋልብም ሳለ ያ ደግ ሰው ተጣርቶ አንተ ሰው ፈረሱንስ ውሰደው ግን እባክህ አንድ ነገር ልንገርህ ስማኝ አለው ሌባውም እየጋለበ ምንድነው እሱ ቢለው ይህን ያረከውን ነገር ማንም ሰው እንዳይሰማው ሰው የሰማ እንደሆነ በእውነት ለታመመና ለወደቀ የደግ ሃሳብ ርህራሄ እንዳያደርግለት ይፈራልና ነው ብሎ ቢነግረው ሌባው በዚህ ነገር ልቡ ተነክቶ ተጸጽቶ ፈረሱን መለሰለት ይባላል:: <<ፍቅር ሁሌ እኔ ምን እሆናለው ሳይሆን ወንድሜ ምን ይሆናል? ነው የሚለው! እንዲህ አይነት ሰው በዚህ ዘመን ይገኝ ይሆን? <<ከከበደ ሚካኤል ታሪክና ምሳሌ 3ኛ መጽሃፍ >>



27 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page